Popular Posts

ዘር የማይቆጥረው መንጌ ኢትዮጵያ ትቅደም



አዲሱ ትውልድ: የቀድሞ መሪ የጓድ ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አፍቃሪዎች ደጋፊና ወዳጆች ቤት 

አያቶቹ አርበኞች አባቱ አርበኛ አጐቶቹ በአድዋ ጦር የወደቁ አርበኞች የኩሩ ነፍጠኛ ልጅ እርሱም ጀግና አገር ወገን ወዳድ የደሀ የጭቁን አባት የሆነው መንጌ በራሱ አንደበት:

"የተወለድኩት ግንቦት 19 1933 ነው:: ልጅ ሆኜ ሲነገረኝ ከነበረው

እንደማስታውሰው <<መንግሥቱ>>
የሚለው ስም የወጣልኝ ከፋሽስት ወረራ በኋላ ነጻነታችን በተመለሰበት ዓመት በመወለዴ ነው:: የተወለድኩት አዲስ አበባ ውስጥ ጊዮርጊስ አጠገብ አሁን ሦስተኛ
ፖሊስ ጣቢያ በሚገኝበት አካባቢ ነው:: አንዲት አነስተኛ የጠላት ሥሪት የነበረች ቤት እዚያ ውስጥ ነው የተወለድኩት::

 የአባቴ አባት አቶ ወልዴ አያና የሸዋ ኦሮሞ ሲሆኑ በግብርና የሚተዳደሩ ነበሩ::  የተወለዱትና የኖሩት ፋሪ አካባቢ ልዩ ስሙ ረጲ በተባለ ቦታ ነበር::

 በጊዜው እንደነበረው የገበሬ ሰራዊት ውስጥ ነፍጠኛ ነበሩ::
 የአሁኖቹ ጠባብ ብሄርተኞች ሊያጥላሉት እንደሚሞክሩት የቃሉን ትርጉም ለማዛባት ከሚመጣ እንጂ ነፍጠኛ ማለት ባለጠመንጃ ማለት ነው::

ነፍጥ ወይም ጠመንጃ ከሚለው የመጣ ነው:: ሌላ ምንም ትርጉም የለውም::
 ነፍጥ መሣሪያው ነው መሣሪያውን ያነገበው ነፍጠኛ ይባላል::

 አባቴም ኃይለማሪያም ወልዴም አርበኛ ነበሩ
ከጠላት ጦር ጋር ከገበሬው ጋር በአርበኝነት
ብዙ ተዋግቶዋል::

በ እናቴ በኩል ስንሄድ አያቷ እናቷና አባቷ
ዘመዶችዋ ሁሉ ተጉለቴዎች ናቸው::

 ይህ የሰሜን ሸዋ ክፍል መሬቱ የተበላ በመሆኑና ከብቱም ቤትደጋጋሚ ችግር እያለቀበት ነዋሪው <<አገር ለማቅናት>> እየተባለ
ወዲያ ወዲህ በማለት ይኖራል:: አገር በምትወረር ግዜም የገበሬ ወታደር እየሆነ ይዘምታል::

 የናቴ አያቷ ወልደአማኑኤል
ጎርፍነህ ይባላሉ:: ሁለት ታላላቅ ወንድሞቻቸው አድዋ ዘምተው በጦር ሜዳ ወድቀዋል:: ወልደ አማኑኤል ጎርፍነህ እራሳቸው ም ዕራብ ሸዋ ውስጥ በባሻ
ማዕረግ የገበሬ ሠራዊት አለቃ ነበሩ 

ከቅርብ ወዳጃቸው የተፃፈ ...

No comments:

Post a Comment

Featured Post

Ragaa MEDIA: Sutuumee yaa sutuumee Maal jaajjata Kottuu mee - Sayyoo Dandanaa @Ragaa MEDIA

Sutuumee yaa sutuumee Maal jaajjata Kottuu mee - Sayyoo Dandanaa @Ragaa MEDIA Ragaa MEDIA is the home old and non archived music, songs and...